|
Page 1 of 3 Information for partners ጎልደን ኦይል አገልግሎት የመንፈቀ-አመት የአገልግሎት ዘገባ ከጥር-ሰኔ 2ዐዐዐ (ጃንዋሪ - ጁን 2ዐዐ8) የክረምት ኮንፈረንሶች በአሜሪካ እንደ አውሮፖዉያን አቆጣጠር 2ዐዐ7 ዓ.ም. ወደ 2ዐዐ8 ሲለወጥ አዲሱን አመት የተቀበልኩት በዴንቨር፤ ኮሎራዶ በምትገኘው የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ቤተክርስቲያን ነበር፡፡ የክረምት አገልግሎቴን የጀመርኩት በቦስተን በምትገኘው የኢትዮጵያውያን ቤተ ክርስቲያን ለ Thanks Giving በተዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ ነበር፡፡ በመቀጠልም በሚሊዋኪ፣ በፊላደሊፈያ፣ በኦክላሆማ፣ በካንሰስ ካገለገልኩ በኃላ በጃነዋሪ 4 2ዐዐ8 ወደ አዲስ አበባ ተመልሻለሁ ፡፡ በአሜሪካ የክረምት ቆይታዬ በቅዱሳን ሕብረተና፣ ክርስቶስን በመምሠል ርእሶች ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን ለመስጠት ችያለሁ፡፡ ጐልደን ኦይል አገልግሎት ከአሜሪካ Internal Revenue Service (IRS) የ 5ዐ1/C/ 3 ፈቃድ አገኘ አገለግሎታችን ከትርፍ ነጻ ሆኖ የሚንቀሣቀስ እንደመሆኑ መጠን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚያደርጋቸው በርካታ እንቅስቃሴዎች እገዛ እንደሚያስፈልገው እሙን ነው፡፡ ለአገልግሎቱ ይህንን ድጋፍ የሚያደርጉ ወገኖች በአሜሪካ ግዛቶች ሁሉ የታክስ ምላሽ ማግኘት ይችሉ ዘንድ አገልግሎታችን ለአሜሪካን መንግስት ባመለከተው መሰረት ከ IRS የ 501(C)3 ፈቃድ አግኝቷል፡፡ ይህንንም በተመለከተ በአሜሪካ በሚገኙ ወገኖች መሃል በስፋት በመንቀሳቀስ የቅዱሳንን መንፈሣዊ እድገት ለማፋጠን ይቻል ዘንድ በአሜሪካ የክረምት ቆይታዬ በ ኦክላሆማ በሚገኘው የአገልግሎቱ ቢሮ የአሜሪካ አስተባባሪያችን ከሆነው ከተወወደው ወንድማችን ከዶ/ር ቢንያም ባይሳ እና ከሌሎች ወገኖች ጋር ሠፊ ወይይት ተካሂዷል፡፡
<< Start < Prev 1 2 3 Next > End >> |
|
Last Updated ( Saturday, 27 March 2010 )
|