|
‹‹አምልኮ›› ሰው የተፈጠረበት አውራ ዓላማ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ከዳር እስከ ዳር ፍንትው አድርጎ ያሣያል፡፡ እግዚአብሔር መመለክ የሚወድ፤ መመለክም የሚገባው፤ አምልኮ ለማይገባው ሲሰጥ የሚቀና ብሎም የሚፈርድ በእውነትና በመንፈስ የሚያመልኩትን ግን ከፈተና የሚጠብቅና የሚባርክ አምላክ መሆኑን ቃሉም ሆነ ታሪክ ይመሰክራል፡፡ ‹‹አምልኮ›› በጉባዔ ውስጥ በሙዚቃ በታጀበ ዝማሬና እልልታ የሚቀርብ ውጪያዊ ገፅታ ቢኖረውም በዋነኝነት ግን በሁሉም የሕይወት አቅጣጫ ያለማቋረጥ የሚተገበር የኑሮ ዘይቤ (lifestyle) ነው፡፡ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዐብይ ርዕስ ላይ ያለዎትን ግንዛቤ ለማሳደግ በአምልኮ ዙሪያ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ የሰፈረውን እውነት እጥር ምጥን ባለ መልኩ የሚተርከውን በቃሉ አገልጋይ በያሬድ ጥላሁን የተፃፈውን ‹‹አምልኮ›› የተሰኘውን መጽሐፍ በማንበብ ሕይወትዎን ይመግቡ፡፡
If you like to order this book "Amlko" by Yared Tilahun, you can order by emailing the link below.
This e-mail address is being protected from spam bots, you need JavaScript enabled to view it
|
|
Last Updated ( Friday, 09 May 2008 )
|