Welcome to Golden Oil Ministries PDF Print E-mail



 (if you want to read the PDF just CLICK here )

  “. . . ዘመኑን ዋጁ! ”

 ሰዎች የጠፋባቸውን ዕቃ ለማግኘት የዕቃውን ዓይነት፣ የጣሉበትን ሥፍራና  ላገኘላቸው ሰው የሚሰጡትን ወሮታ ገልፀው ማስታወቂያ በሚለጥፉበት የአፋልጉኝ ሰሌዳ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ይነበባል፡፡

“ትናንት፤ በፀሐይ መውጣትና መጥለቅ መካከል ወርቅ የሆኑና እያንዳንዳቸው በስልሳ፤ ደቂቃዎች ያሸበረቁ ሁለት ሰዓታት ጠፍተውብኛል፡፡ ላገኘልኝ ሰው የምከፍለው ምንም ወሮታ የለም፤ ዳግም ላይገኙ ለዘላለም ጠፍተዋልና፡፡”

የሚል፡፡ ይህ ማስታወቂያ አንድ ሰው  ከአንድ ቀን በፊት ስላባከናቸው ሁለት ሰዓታት የጻፈው ፀፀት አዘል አቤቱታ ነው፡፡[1]

አበው እንደሚሉት ‹‹ጊዜ ወርቅ›› ነው፡፡ ነገር ግን እንደ ወርቅ አይገዛም፣ አይሸጥም ወይም አይለወጥም፤ በባንክ አይቀመጥም ወይም ለሌላ ሰው በብድር አይሰጥም፡፡ ጊዜ በጊዜ ውስጥ ጥቅም ላይ ካልዋለ በስተቀር ይባክናል፤ ለዘላለምም ይጠፋል፡፡ በዚህ ምድር ላይ ለሁሉ እኩል የተሰጠ ነገር ቢኖር ጊዜ ብቻ ነው፡፡ የማይክሮ ሶፍት ባለቤት ቢል ጌት እና አንድ የጎዳና ተዳዳሪ እኩል ሃያ አራት ሰዓታት፤ እኩል ሰባት ቀናት እንዳላቸው ማሰብ አያስገርምም? ሁለቱ በጊዜ አጠቃቀም እንጂ በጊዜ መጠን አንዱ ከሌላው በሰኮንድ እንኳ ፈፅሞ አይበላለጡም፡፡ ጊዜ ዕድል ነው፡፡ ታዲያ ቁም ነገሩ ባለ ዕድል መሆን ብቻ ሳይሆን ዕድልን በአግባቡ በመጠቀም ሊደረስ የሚገባው ሥፍራ መድረስ ነው፡፡ ጊዜ ሕይወት ነው! በሕይወት እስካለን ድረስ ጊዜ አለን፤ በምድር ላይ ጊዜ የማይኖረን ከምድር ስንለይ ብቻ ነው፡፡ ጊዜ ልንጠቀምበት የምንችል ሃብት ብቻ ሳይሆን፤ የምንጠየቅበትም ኃላፊነት ነው፡፡ ታዲያ በዐይናችን ፊት በቅፅበት እየከነፈ ስላለው ጊዜያችን ምን እያሰብን ይሆን?

በጅማሪዬ ላይ ስለ ጊዜ ይህን ያልኩት ያለምክንያት አይደለም፡፡ የፈረንጆቹ 2008

ለ 2009 ስፍራ ሊለቅ ጥቂት ቀናት በቀሩበት በዚህ ወቅት ስለጊዜ አጠቃቀም ብርሃን ሊፈነጥቅልን የሚችል ሃሳብ ከኤፌሶን 5፡-15-21 ላካፍላችሁ ከጅዬ ነው፡፡


Last Updated ( Friday, 10 April 2009 )
 
< Prev